በኳታር የሚገኘው የአሜሪካ ጦር ለአሜሪካ ወታደሮች እጅግ አስፈላጊ ነው ተባለ

Date:

ትራምፕ በኳታር የሚገኘው የአሜሪካ  የጦር ሰፈር በአሜሪካ እና በኳታር መካከል ያለው የስትራቴጂክ ግንኙነት ቁልፍ አካል ነው።ከአንድ አመት በፊት ሁለቱ ሀገራት የመሠረቱት ስምምነት ለቀጣዮቹ 10 አመታት ለማራዘም ወስነዋል። 38 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስት ለማድረግ የማሰብ ስምምነትን ተፈራርመዋል።

ከወታደራዊ እይታ አንጻር በመካከለኛው ምስራቅ ለሚንቀሳቀሱ የአሜሪካ ወታደሮች መሰረቱ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። የስለላ መረጃን በመሰብሰብ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለዉ፡፡ በሌላ በኩል የኳታር አየር መንገድ 210 ያህል 787 ድሪምላይነር እና 777 ኤክስ አውሮፕላኖችን በ96 ቢሊየን ዶላር ለመግዛት ከቦይንግ ጋር ያደረገውን ስምምነት ትረምፕ በዶሃ በመገኘት “ታሪካዊ” ሲሉ አሞካሽተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የኢነርጂ ፀሐፊ ክሪስ ራይት ከፕሬዚዳንቱ ጋር በመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝታቸው ላይ ካሉት የትራምፕ ካቢኔ አባላት መካከል አንዱ ናቸው።ሐሙስ ዕለት በኤክስ ላይ በለጠፉት ጽሁፍ ራይት በሳዑዲ አረቢያ የትራምፕን ንግግር ዋና ጭብጥ በድጋሚ አንስተዋል፡፡ በክልሉ ውስጥ ያሉ አዲስ ትውልድ መሪዎች ሰላማዊ እና የበለፀገ የወደፊት ሁኔታ ለመፍጠር የቆዩ ግጭቶችን እና መከፋፈልን መሻገር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡”ፕሬዚዳንት ትራምፕ ፍጹም ትክክል ናቸው፤ የመካከለኛው ምስራቅ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ንግድ እንጂ ትርምስ አይደለም” ሲሉ ራይት ጽፈዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...