ለሊጉ ዋንጫ እና ለአውሮፓ ተሳትፎ ብርቱ ፉክክር እየተደረገበት የሚገኘው የጣልያን ሴርያ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት በተመሳሳይ ሰዓት ተደርገዋል።
በምሽቱ ጨዋታዎች ወቅት አምስት አሰልጣኞች በዳኛ ቀይ ካርድ ተመዞባቸው ከሜዳ ለመውጣት ተገደው ነበር።
የናፖሊው ዋና አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ እንዲሁም የተጋጣሚያቸው ፓርማ አሰልጣኝ ክሪስቲያን ቺቩ ቀይ ካርድ ተመዞባቸዋል።
ኢንተር ሚላን ከላዝዮ ባደረጉት ጨዋታ አሰልጣኝ ሲሞን ኢንዛጊ እና አሰልጣኝ ማርኮ ባሮኒ ቀይ ካርድ ተመልተዋል።
በተጨማሪም የኤሲ ሚላኑ ዋና አሰልጣኝ ሰሬጂዮ ኮንሴሳኦ ቀይ ካርድ የተመለከቱ ሌላኛው አሰልጣኝ ናቸው።
ሁሉም አሰልጣኞች የሴርያው የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር ያመልጣቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።
@tikvahethsport
