የሁዋጂያን ኢንዱስትሪ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አምራችነት ቀዳሚ ከሆኑ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው የቻይናው የጓንግዙ አውቶሞቢል ኩባንያ (ጂኤሲ) ምርቶችን በኢትዮጵያ ለማቅረብ የሚያስችለውን የመኪና ሞዴል የማስተዋወቅ መርሃግብር አካሂዷል።ኩባንያው በመርሃ ግብሩ AION Y and ES9 የተሰኙ ሁለት የኤለኢክትሪክ ተሽከርካሪ ሞዴሎችን ማስተዋወቁን ገልጿል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን፣ “የኢትዮጵያ መንግስት በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖችን ማምረት፣ ማስመጣትና መገጣጠም በመከልከሉ፤ ሀገሪቱ እንደ ጂኤሲ ላሉ ታዋቂ ኩባንያዎች ምቹ ገበያ ትሆናለች” ብለዋል።የትራንሰፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ደኤታ አቶ በርኦ ሀሰን በበኩላቸው፤ የኩባንያው ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ለሁለቱ ሀገሮች የንግድ ትስስር ትልቅ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።
አክለውም መንግሥት ለኤሌክትሪክ አውቶሞቢል አቅራቢዎች ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቅሰው ኩባንያው ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መግባቱ ሰፊ የገበያ ዕድል እንደሚፈጥርለት ገልጸዋል።
የሁአጂያን ሊቀመንበር ዣንግ ሁአሮንግ በበኩላቸው፤ ኩባንያው በቀጣይ የኤሌክትሪክ መኪኖችን በኢትዮጵያ ለማምረት እቅድ የያዘ መያዙን እና ይህም ኢትዮጵያንና ቻይናን ይበልጥ በንግድ ለማጠናከር እንደሚረዳ ተናግረዋል።
