የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን ሞሀመድ አብዱላሂ ኢሮ ከ130 በላይ ለሚሆኑ ሀገራት ለሶማሊላንድ እውቅና እንዲሰጡ ጥሪ ማቅረባቸውን ገለጹ።
ሶማሊላንድ ነጻነቷን ያወጀችበት 34ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንቱ ጠቅላይ ሚኒስትሮችን ነገሥታትን እና አሚሮችን ጨምሮ ከ130 በላይ ለሚሆኑ ሀገራት ለሶማሊላንድ እውቅና እንዲሰጡ የሚጠይቅ የፕሬዚዳንታዊ ደብዳቤዎችን መላካቸውን ተናግረዋል።
ክብረ በዓል ላይ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና እንዲሰጥ በድጋሚ ጠንካራ ጥሪ ማቅረባቸውን ሆርን ዲፕሎማት ዘግቧል።
ፕሬዝዳንት ኢሮ ኢትዮጵያን፣ የተባበሩትአረብኤምሬትስ፣ ዩናይትድ_ኪንግደም፣አሜሪካ፣ጂቡቲ ታይዋን፣ ቱርክ እና ኬንያን ጨምሮ ከሶማሊላንድ ጋር በወዳጅነት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት እና ትብብር ላላቸው ሀገሮች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በሰላም፣ በጋራ መከባበር እና በገንቢ አጋርነት መርሆዎች ላይ የተመሰረተ መሆኑን አረጋግጠው“ በአፍሪካ ቀንድ እና በቀይ ባህር ላይ ብልጽግናን በማጎልበት እና በቀጠናዊ ደህንነት ውስጥ ወሳኝ ሚና ለመጫወት ዝግጁ ነን” ብለዋል።
