በአማራ ክልል የተመረተ ከ20 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ ኦፓል ለውጭ ገበያ ቀረበ

Date:

በአማራ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተመረተ ከ20 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የኦፓል ማዕድን በማዕከላዊ ገበያ በኩል ለውጭ ገበያ መቅረቡን የክልሉ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

ለውጭ ገበያ ከቀረበው የኦፓል ማዕድን ምርት ከ7 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የቢሮው ኃላፊ ኃይሌ አበበ ተናግረዋል፡፡

በቀሪው ሩብ የበጀት ዓመትም እሴት የተጨመረበት የኦፓል ምርት ለማቅረብ ጥረት እየተደረገ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በክልሉ ያለውን የማዕድን ሃብት በማልማት ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶችን በመሳብና በመደገፍ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከኦፓል ምርቱ በተጨማሪ 76 ኪሎ ግራም የወርቅ ምርት ለብሔራዊ ባንክ መቅረቡንም ጠቁመዋል፡፡

ባለፈው በጀት ዓመት በክልሉ ተመርቶ በማዕከላዊ ገበያ በኩል ወደ ውጭ ከተላከው የኦፓል ምርት ከ2 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የክልሉ የማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...