በአጼ ምንሊክ ዘመን የተሰራ ታሪካዊ ጎራዴ የኖርዌይ ዜግነት ካላቸው ፕሮፌሰር ጉናር /Gunnar Aksel Bjune/ ከባለቤታቸው ክርስቲን ለኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ተበርክቷል።
ጎራዴውን በ1974 ዓ.ም በግዢ እንደተገኘ የተገለጸ ሲሆን እስከ አሁን በጥንቃቄ ቤታቸው ተጠብቆ ይገኝ እንደነበረ በርክክቡ ወቅት ተገልጿል። ቅርሱን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ተረክበዋል።
ረዳት ፕሮፌሰር አበባው ጉራዴው ከመቶ አመት በላይ እድሜ ሊኖረው የሚችልና የኢትዮጵያ የነጻነት ተምሳሌት የሆነውን ይህን ቅርስ ለባለስልጣኑ በመለገሳቸው ደስታ እንደሰማቸው ገልጸዋል።
ቅርሱ ለባለስልጣኑ እንዲሰጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉት ለፕሮፌሰር ካሳሁን ፣ ዶ/ር አለምሰገድ እና ለዶ/ር አሉላ ፓንክረስት ምስጋና አቅርበዋል። ዋና ዳይሬክተሩ ለፕሮፌሰር ጉናርና ባለቤታቸው የምስጋና የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል።
