የትግራይ ነፃነት ፓርቲ የሁለቱን የህወሓት አንጃዎች አቋም ተቃወመ

Date:

የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ(ህወሓት) ሁለት አንጃዎች በየፊናቸዉ ከኢትዮጵያ እና ከኤርትራ መንግሥታት ጋር ለመተባበር እየጣሩ መሆናቸዉን የትግራይ ነፃነት ፓርቲ ተቃወመ።የትግራይ ነፃነት ፓርቲ  መሪዎች እንዳሉት ሁለቱ አንጃዎች ከአዲስ አበባና ከአሥመራ ጋር ለመሥራት በየፊናቸዉ የሚያደርጉት ተቃራኒ ጥረት አደገኛ ነዉ።የኢትዮጵያ የፌደራል መንግስት የፕሪቶርያውን ስምምነት በሙሉ  ገቢራዊ እንደሚያደርግም ፓርቲዉ ጠይቋል።

ህወሓት ውስጥ የተፈጠረው መከፋፈል ተከትሎ ሁለቱ የፓርቲው ቡድኖች አስመራ እና አዲስአበባ ካሉ ሐይሎች ጋር እየሰሩ ትግራይን ወደ ከፋ ችግር እየመሩ ነው ያለው በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሐን መግለጫ የሰጠው የትግራይ ነፃነት ፓርቲ፥ ካለፈው ጦርነት ያላገገመችው ትግራይ በነዚህ ሐይሎች እንዲሁም ከእነሱ ጋር እየተወዳጁ ባሉ የህወሓት ሁለት ቡድኖች ምክንያት በሌላ ዙር ጦርነት ስጋት ላይ ናት ሲሉ የትግራይ ነፃነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር ደጀን መዝገበ ተናግረዋል።

የትግራይ ነፃነት ፓርቲ ኢትዮጵያ ኤርትራ ገብተውበት ባለው ውጥረት ዙርያ የትግራይ የፖለቲካ ሀይሎች ገለልተኛ መሆን አለባቸው ብሎ እንደሚያምን ያስታወቀ ሲሆን፥ ትግራይ በኢትዮጵያ ሕግ አውጪ ተቋም ጨምሮ በአጠቃላይ ፌደረሽኑ ውክልና የላትም፣ ኤርትራ ደግሞ ሌላ ሀገር ነው ሲሉ ‘ገለልተኛ አቋም መያዝ’ ለሚል ሙግት እንደ ምክንያት አቅርቧል። 

ከዚህ በተጨማሪ በቅርቡ በተገለፀው የህወሓት ከፖለቲካ ፓርቲነት መሰረዝበኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ መሰረዝ ዙርያ አስተያየታቸው የሰጡት የትግራይ ነፃነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር ደጀን መዝገበ፥ የህወሓት መሰረዝ የሚያፈርሰው የሰላም ስምምነት የለም ብለዋል። የትግራይ ነፃነት ፓርቲ በትግራይ ያለው ስርዓት በመቃወም ሰፊ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
Dw Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...