የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የዲጂታል ክፍያዎችን እና የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማሳደግ የክፍያ ስርዓት መመሪያውን ማሻሻሉን አስታዉቋል።
ማዕከላዊ ባንኩ “የክፍያ መፈጸሚያ ሰነድ አውጪዎች ፈቃድ እና እውቅና አሰጣጥ መመሪያውን” ያሻሻለ ሲሆን በዘርፉ ፍቃድ ለመዉሰድ ይጠይቅ የነበረዉ 50 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል አሁን ወደ 100 ሚሊዮን ብር ከፍ ብሏል።
በሥራ ላይ የዋለው አዲሱ መመሪያ ቁጥር ONPS/10/2025፣ አሁን ፈቃድ ያላቸው የክፍያ ሥርዓት ኦፐሬተሮች ካፒታላቸው ከዚህ መጠን በታች ከሆነ እኤአ እስከ ሰኔ 2027 መጨረሻ ድረስ ይህንን መስፈርት እንዲያሟሉ ተጠይቀዋል።
በፈቃድ አሰጣጥ ሂደት ላይ ያሉ ደግሞ ፈቃዳቸውን ከተቀበሉ በሁለት ዓመት ውስጥ አዲሱን የካፒታል እና የአክሲዮን ድርሻ መስፈርቶች ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው ካፒታል ለመረዳት ችሏል።
