በኢትዮጵያ የአጫሾች ቁጥር ከ5 በመቶ ወደ 4 ነጥብ 6 በመቶ ዝቅ ማለቱ ተገለጸ

Date:

በኢትዮጵያ አጠቃላይ የአጫሾች ቁጥር ከ5 በመቶ ወደ 4 ነጥብ 6 በመቶ ዝቅ ማለቱን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ባለስልጣኑ አገር አቀፍ የአዋቂዎች ትምባሆ አጠቃቀም የዳሰሳ ጥናት ከባለድርሻ አካላት ጋር እንዳካሄደ እና፤ በቅርቡ በተጠናቀቀው 2ኛ ዙር ጥናት የአዋቂዎች የአጫሽነት መጠን መሻሻሉን ገልጿል፡፡

በዚህም መሠረት፤ በኢትዮጵያ አጠቃላይ የትምባሆ ተጠቃሚዎች ቁጥር 5 በመቶ የነበረ ሲሆን፤ በቅርብ ጊዜው ጥናት ወደ 4 ነጥብ 6 በመቶ ዝቅ ማለቱን አሐዱ ከተቋሙ ያገኘው መረጃ ያሳያል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዓለም አቀፍ የትምባሆ ቁጥጥር ማዕቀፍ እ.ኤ.አ በ2005 ተቀብሎ በአዋጅ ቁጥር 1112/2011 ጠንካራ የሆኑ የትንባሆ ቁጥጥር አንቀፆችን በማካተት የተለያዩ ሥራዎችን ከአጋር አካላት ጋር በመሆን ሲሰራ መቆየቱን አስታውቋል።

በዚህም መሠረት አገር አቀፍ የትንባሆ ቁጥጥር አስተባባሪ ኮሚቴ በማቋቋም እና የ8 ዓመት አገር አቀፍ የትንባሆ ቁጥጥር ስትራቴጅክ እቅድ በመንደፍና ከክልል ተቆጣጣሪ አካላት ጋር በመቀናጀት እየተሰራበት ነው ብሏል።

የተከለከለ ይዘት ያለውን ትምባሆ፣ ሺሻ፣ የኤሌክትሪክ ኒኮቲን መስጫ መሳሪያ ወይም ሌላ ማንኛውንም ተመሳሳይ ምርት ያመረተ፣ ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባ፣ ያከፋፈለ፣ ያከማቸ ወይም የሸጠ በአዋጅ ቁጥር 1112/2011 መሠረት እስከ ሦስት ዓመት በሚደርስ እስራት እና እስከ 200 ሺሕ ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እንደሚያስቀጣ ተገልጿል።

ዘንድሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ38ኛ ጊዜ በአገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ33ኛ ጊዜ ግንቦት 23/2017 የሚከበረውን በዓለም ትምባሆ የማይጨስበት ቀን የዓለም ጤና ድርጅት “በትምባሆ እና ኒኮቲን ምርቶች ላይ የትምባሆ ኢንዱስትሪ አሳሳችና ድብቅ ስልቶችን በማጋለጥ ወጣቶችን እንታደግ” በሚል መሪ ቃል እንዲከበር ወስኗል።

የዘመቻው አላማም የትምባሆ እና የኒኮቲን ኢንዱስትሪዎች ጎጂ ምርቶቻቸውን ማራኪ ለማስመሰል የሚጠቀሙባቸውን ዘዴዎች በማጋለጥ ላይ እንዲያተኩር ታስቦ ነው ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...