ፑቲን ወደ ቻይና

Date:

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን የሁለተኛውን ዓለም ጦርነት ድል በቻይና ለማክበር ወደ ቤይጂንግ  ሊያቀኑ ነው፡፡

ቻይና ጃፓን እጅ የሰጠችበትን መስከረም ወርን ከሌሎቹ አሸናፊ አገራት በተለየ የድል ቀን አድርጋ ታስበዋለች።

ፕሬዚዳንት ፑቲን በ1945 ሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተጠናቀቀበትን 80ኛ ዓመት የድል በዓል ከሺ ጂንፒንግ ጋር በድጋሜ ቻይና ላይ ያከብራሉ፡፡

ቤይጂንግ ቶኪዮ የተሸነፈችበትን  ከሞስኮ የድል በዓል በወራት ልዩነት መስከረምን የድል በዓሏ አድርጋ  እንደምታስብ ይታወቃል።

የሩሲያ ብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ሀላፊ ሰርጌይ ሾይጉ“ሺ ወደ ሞስኮ እንደመጡት ሁሉ ፑቲንም ወደ ቤይጂንግ ለድል በዓሉ ያቀናሉ” ብለዋል፡፡

ሞስኮ የፈረንጆቹን ግንቦት ዘጠኝን የድል በዓሏ አድርጋ ስታከብር ቤይጂንግ ጃፓን ተሽንፋ የሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኤዥያ ምድር የተጠናቀቀበትን መስከረም ሶስትን የድል በዓል አድርጋ  ታከብራለች፡፡

የቻይናን እና የሩሲያን የጠበቀ ትስስር የሚያሳይ ጉብኝት ይሆናልም ተብሎ ይጠበቃል የፑቲን ጉዞ፡

አገራቱ በስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ አብረው በአንድ መድረክ በመሰለፍ የዓለምን ፖለቲካ ለመቃኘት በመስራት ላይ መሆናቸውንም አስታውሰዋል ሽይጉ።

ቤይጂንግና ሞስኮ ገደብ የለሽ አጋርነትን በመመስረት ሁለንተናዊ ግንኙነታቸውን አጠናክረው መቀጠላቸው ይታወሳል ሲል የዘገበው አር ቲ ነው፡፡

Nbc_Ethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...