የኢትዮጵያ የዕቃ አስተላላፊዎችና የመርከብ ወኪሎች ማህበር እና የብሪታኒያ ዓለም አቀፍ የጭነት አስተላላፊዎች ማህበር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል ፡፡
በስነስርዓቱ ላይ እንደተገለጸው በኢትዮጵያ የሎጀስቲክ ዘርፍ ያለበት ደረጃ እጅግ በጣም ዝቅተኛ ኋላቀር ነው ፡፡
ለዚህ እንደምክንያት የተገለጸው ደግሞ ኢትዮጵያ የራሷ የባህር ወደብ የሌላት በመሆኑ በዘርፉ ላይ ከፍተኛ ጫና ሊፈጥር ችሏል ፡፡
አቶ ዳዊት ውብሸት የኢትዮጵያ ዕቃ አስተላላፊዎችና የመርከብ ወኪሎች ማህበር ፕሬዝዳንት እንዳስታወቁት ኢትዮጵያ በዘርፉ በዘላቂነት ተጠቃሚ እንድትሆን የባህር በር ጉዳይ ውሳኔ ማግኘት አለበት ፡፡
ሁለቱ አቻ ማህበራትን የኢትዮጵያ የሎጀስቲክ ዘርፍ ዘመናዊና ተወዳዳሪ ለማድረግ በአቅም ግንባታ ፣የልምድ ልውውጥና ተያያዥ ስራዎችን በጋራ ለመስራት ስምምነት መፈጸማቸው ተናግረዋል ፡፡
