ወጣቱ ኢትዮጵያዊ የዓለም የሰላም አምባሳደሮች ሽልማት በስቶኮልም ተጎናፀፈ

Date:

ወጣቱ ኢትዮጵያዊ የሰላም አምባሳደር ስለሺ ዑመር የዓለም የሰላም አምባሳደር ሽልማት አሸናፊ በመሆን ሀገሩንና ህዝቡን በትልቅ መድረክ አስጠርቷል።

ወጣቱ ሽልማቱን ያሸነፈው ሰሞኑን ሲዊድን ስቶኮልም በተካሄደ ትልቅ ስነስርዓት ነው።

ወጣቱ የሰላም አምባሳደር ይህንን ትልቅ የሰላም አምባሳደርነት ሽልማት አሸናፊ የሆነው ፤ በሰላም፣ በዲፕሎማሲ፣በወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት፣በስብዕና ግንባታና ተያያዥ መስኮች እያከናወነ ባለው ስኬታማ ስራ ሲሆን ሽልማቱም በሰላምና በተያያዥ ጉዳዮች ስኬታማ ስራ ላከናወኑ ግለሰቦችና ተቋማት በስቶኮልም የሚሰጥ ሽልማት መሆኑ ታውቋል።

አምባሳደር ስለሺ ዑመር በዓለም አቀፍ የሰራተኞች ድርጅት (lLO)፣በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ( UNHCR) እና በተባበሩት መንግስታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) የወጣቶች መረብ ሊቀመንበር ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት አባልም ነው።

ወጣት አምባሳደር ስለሺ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ)፣ በአፍሪካ ሕብረትና በብሪክስ የወጣቶች ካውንስል ለሐገሩ በሰላም፣ በኢኮኖሚና በፖለቲካዊ ተሳትፎው ትልቅ ድልን እየተጎናፀፈ የሚገኝ ወጣት መሪ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።

የሰላም አምባሳደሩ ወጣት ከዚህም በተጨማሪ ከተመሰረተ ሰባት ዓመታትን ያስቆጠረውና በወጣቶች መሪነት፣ በዲፕሎማሲ፣ በስራ ፈጠራና በተያያዥ ዘርፎች ላይ አተኩሮ የሚሰራው የ “Safe Light Initiatives” ሀገር በቀል ሲቪል ማህበር መስራችና ዳይሬክተርም ነው።

ወጣቱ በስቶኮልም ያሸነፈው የሰላም አምባሳደርነት ሹመት ለኢትዮጵያ ወጣቶች መነቃቃትን የሚፈጥርና ምሳሌ የሚሆን ነው ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...