ከ800 በላይ ጠበቆችና ዳኞች በእስራኤል ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ጥሪ አቀረቡ

Date:

ቪኦኤ እንደዘገበው፤ ከ800 በላይ  የህግ ባለሙያዎች፣ ምሁራንና የቀድሞ ዳኞች  እንግሊዝ በእስራኤል መንግሥት  ላይ ማዕቀብ እንድትጥል  ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የፍትህ አካላቱ ባለፈው ሰኞ  ለጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመር በላኩት ግልጽ ደብዳቤ፣ የእንግሊዝ  መንግስት እስራኤል እየፈጸመች ያለውን “ከባድ የአለም አቀፍ ህግ ጥሰቶች” ለማስቆም ተጨባጭ እርምጃ መውሰድ አለበት ብለዋል፡፡

“በጋዛ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈፀመ ነው ወይም ቢያንስ  የዘር ማጥፋት ከፍተኛ አደጋ አለ” ብለዋል፤ በደብዳቤያቸው፡፡ 

በጋዛ የፍልስጤም ህዝብ ላይ የሚደርሰውን ውድመት ለመከላከል አስቸኳይና ወሳኝ እርምጃ እንደሚያስፈልግ የሚጠቁመው ደብዳቤው፤ ስታርመር አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡ ማሳሰቡን ዘገባው አመልክቷል፡፡

የእስራኤል የገንዘብ ሚኒስትር ቤዛሌል ስሞትሪች በቅርቡ የሰጧቸውን  አስተያየቶች በመጥቀስም፣ እስራኤል “የጋዛ ሰርጥ ግዛትን በሙሉ ለመቆጣጠርና  ለማጽዳት እንዲሁም  ሃማስ እስኪጠፋ ድረስ ለመቆየት” ያላትን  ፍላጎት ጠቁሟል፡፡

በቀጠለው የእስራኤል ጥቃት በጋዛ ሰርጥ በሚገኙ ሆስፒታሎች ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ቢያንስ 79 ሰዎች ሲገደሉ፣ 163 ያህሉ ደግሞ ቆስለዋል። አሃዙ ጦርነቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የተገደሉትን ሰዎች ቁጥር ወደ 54ሺ 56 ያደረሰው ሲሆን፤ 123ሺ 1መቶ 29 ሰዎች ቆስለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...