ላለፉት 12 ቀናት በስራ ማቆም አድማ የቆዩት የመቐለ ዳኞች ስራ ለመጀመር መግባባት ላይ መደረሳቸው ተነግሯል።
ዳኞቹ ያቀረቡት የደህንነት ስጋት ጥያቄ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚከታተለው በተደረሰው ስምምነት ምክንያት ነው ወደ ስራ ገበታቸው ለመመለስ የወሰኑት።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ” ዳኞቹ ያለባቸው የድህንነት ስጋት በማስመልከት ከፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) እና ከፍትህ አካላት አመራሮች ጋር ተወያይተዋል ” ብሏል።
” በውይይቱ በዳኞቹ ላይ ያንዣበበው የደህንነት ስጋት በጥልቀት ተዳሷል ፤ ችግሩን ከስሩ በመረዳት ለመፍትሄው ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ” ሲል ገልጿል።
” የደህንነት ስጋቱ በዘላቂነት ለመፍታት የአጭርና የረጅም ጊዜ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል። በተደረሰው መግባባት መሰረት የመቐለ ሰባቱ ክፍለ ከተማ ፍርድ ቤቶች ከዛሬ ግንቦት 21/2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስራ ገበታ ይመለሳሉ ” ብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
