ብፁዕ አቡነ አብርሃም የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሦስት ዓመታት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅነት የአገልግሎት ጊዜያቸውን አጠናቀው ወደ ሀገረ ስብከታቸው መመለሳቸውን ምክንያት በማድረግ በባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።
በአቀባበሉ ከሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጀምሮ የተለያዩ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን፣ በርካታ ኦርቶዶክሳውያን ተገኝተዋል።
የአቀባበል ሥርዐቱ በባሕር ዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል መንበረ ጵጵስና የቀጠለ ሲሆን የተለያዩ መርሐ ግብራትን በማቅረብ እየተከናወነ ይገኛል።
©ፈለገ ገነት ሚዲያ
