ኢትዮጵያዊቷ ቆንጆ ከአፍሪካ 1ኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቀቀች

Date:

በህንድ እየተከናወነ ያለው ሚስ ወርልድ የቁንጅና ውድድር አሁን ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ በዚህ ውድድር የ109 አገራት ቆነጃጅት የተሳተፉ ሲሆን ‹‹ሚስ ወርልድ›› የሚል መጠሪያ በማግኘት የዘንድሮውን ዘውድ የጫነችው ታይላንዳዊቷ ኦፓል ሱቻታ ሆናለች፡፡

እሷን ተከትላ ኢትዮጵያን የወከለችውና በውድድሩ ላይ ‹‹ሚስ ኢትዮጵያ›› ተብላ ስትጠራ የነበረችው ሀሴት ደረጄ 2ተኛ ሆናለች፡፡ ሀሴት ከአለም 2ተኛ ትሁን እንጂ ከአፍሪካ 1ኛ በመሆን ከአህጉሪቱ ቆነጃጅት ሁሉ ቀዳሚ በመሆን አሸናፊ መሆኗን የውድድሩ አዘጋጆች አስታውቀዋል፡፡

ከአለም 3ተኛ የወጣችው የፖላንድ ተወዳዳሪዋ ስትሆን የማርቲንኪ ተወዳዳሪዋ 4ተኛ ሆናለች፡፡ ይህ ውድድር ለአንድ ወር በህንድ የተለያዩ ግዛቶች ሲከናወን የቆየ ሲሆን ውድድሩን ዘሀበሻ ሲዘግብላችሁ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

MissWorld2025 #MissEthiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...

የብሔር ፌደራሊዝምን ለማስቀጠል “የቆረጡ” ተመካካሪዎች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 14ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች የአጀንዳ...

“የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው” ፓትርያርኩ

የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው...