የጀግናው አባት ማስታወሻ ለልጅ

Date:


ዛሬ ከፒኤስጂ ጋር የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ያሸነፉት አሠልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ በሕይወት ስለሌለችው ልጃቸው ብዙ ጊዜ ሲናገሩ ነበር።

“አስታውሳለሁ ልጄ ከባርሴሎና ጋር የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ሳነሣ አብራኝ ደስታዬን ተካፍላለች። ነገር ግን እርሷ የተፈቀደላት 9 ዓመት ብቻ ነውና ሔዳለች። ግን እርሷ ሕያው ነች፤ ለእርሷ ማስታወሻ የሚሆነኝ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ነው” ይሉ ነበር።

የአሠልጣኝ ሊዊስ ኤንሪኬ ሴት ልጅ ዣና በካንሰር ሕመም ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየች 6 ዓመታት አለፉ።

“ለልጄ መታሰቢያ የሻምፒዮንስ ሊጉ ዋንጫ ያስፈልገኛል፤ ይህን እንዳሳካው ዣናን ማሰቡ በቂዬ ነው፤ ምክንያቱም እርሷ ሁሌ በመንፈስ ከኔጋ ስላለች” ይላሉ አሠልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ።

እርሳቸው እንዳሉትም አልቀረም፤ ፒኤስጂን ይዘው ኢንተር ሚላንን አሸንፈው ታላቁን ዋንጫ ለልጃቸው ማስታወሻ አደረጉት።

ጀግናው አባት ሊዊስ ኤነሪኬ ለልጃቸው ዣና ያበረከቱት ታላቁ ስጦታ አውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ነው።

ልጃቸው እንዳልተለየቻቸው የሚናገሩት ስፔናዊው ታክቲሽያን፣ “ዣና 9 ዓመታትን ሰጥታናለች” ይላሉ።

ዣና የአባቷ ክለብ ድል ባደረገበት በዛሬው ዕለት ታስባለች።

በሀብተሚካኤል ክፍሉ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...

የብሔር ፌደራሊዝምን ለማስቀጠል “የቆረጡ” ተመካካሪዎች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 14ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች የአጀንዳ...

“የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው” ፓትርያርኩ

የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው...