ከቀናት በፊት ሃሴት ባስመዘገበችው ድንቅ ብቃት ስንደሰት ሳንጨርስ፣ አሁን ደግሞ ቶማስና ታምራት በ2025 American’s Got Talent ውድድር ላይ ኢትዮጵያን በአደባባይ አስከብረዋል።
የሳይመን ኮዌል አድናቆት
እነዚህ ወጣት ኢትዮጵያውያን ተሰጥኦአቸውን ያሳዩት በአለም ታዋቂ በሆነው የAmerican’s Got Talent መድረክ ላይ ሲሆን፣ በተለይም አንጋፋው ዳኛ ሳይመን ኮዌል ትርኢታቸውን “የዓመቱ ምርጥ ትርኢት” (The Best Act of The Year) ሲል አሞካሽቷል።
የትም ሲሄዱ “ከኢትዮጵያ” ብለው በኩራት የሚናገሩት እነዚህ ባለድንቅ ተሰጥኦዎች፣ መድረኩ ላይ ያሳዩት ብቃት እጅግ አስደናቂ ነበር።
የማይታመን ብቃትና የዳኞች ምላሽ
ቶማስ፣ ከታምራት እግሮች ላይ በመተጣጠፍ፣ አንድ ሰው ሊያደርገው ይችላል ተብሎ በማይታሰብ ፍጥነትና የአክሮባት እንዲሁም የጂምናስቲክ እንቅስቃሴዎች አሳይቷል።
ይህ አስገራሚ ችሎታቸው አራቱን ዳኞችና በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎችን አስገርሞ፣ ሁሉም ቆመው በጭብጨባ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
ሳይመን ኮዌል በAmerican’s Got Talent ታሪክ እንዲህ አይነት ልዩ ተሰጥኦ አይቶ እንደማያውቅ በመግለጽ፣ ሁለቱ ኢትዮጵያውያን የ2025 የውድድሩ ዋነኛ ድምቀቶች እንደሚሆኑ ተናግሯል።
ሌሎች ዳኞችም በብቃታቸው መደነቃቸውን ገልጸው፣ በአንድ ድምፅ ወደ ቀጣዩ ዙር እንዲያልፉ ድምፃቸውን ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያን በመወከል ኩራት
በተመልካች ብዛትም ሆነ በዝግጅት ደረጃ የአለማችን ቀዳሚ በሆነውና ለመወዳደር ከፍተኛ ብቃት የሚጠይቀው በዚህ መድረክ ላይ፣ ኢትዮጵያን ወክላችሁ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋችሁ ትልቅ ኩራት ነው።
ቶማስ እና ታምራት እንኳን ደስ አላችሁ! በእናንተ በጣም ኮርተናል፣ በቀጣይ ለምታደርጉት ጉዞ
መልካም ዕድል እንመኛለን።
©️የኔታ ቲዬብ
