የሚድሮክ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አሕመድ እንደገለጹት የግሉ ዘርፍ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በማሳደግ ረገድ ጉልህ ድርሻ አለው ፡፡
ሚድሮክ በጅማና በኢሉባቦር አራት ሺህ ሄክታር መሬት ላይ አንድ ሺህ አርሶ አደሮችን አደራጅቶ ከፍተኛ የሻይ ቅጠል ምርት እያመረተ ይገኛል። ከሚመረተው ምርት 20 በመቶ ለውጭ ገበያ ያቀርባል ሲሉ አቶ ጀማል ገልጸዋል ፡፡
ነገር ግን በአካባቢው ከ150 ሺህ አርሶ አደሮች በላይ በቆሎ እያመረቱ በትንሽ ገቢ በድህነት እየኖሩ ይገኛሉ ያሉት አቶ ጀማል፤ የሻይ ምርትን ለማሳደግና ገቢን ለመጨመር የኦሮሚያ ክልል በ30 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሻይ ምርት ለማምረት እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።
ለዚህም ሚድሮክ የሙያ እገዛ፣ የችግኝ አቅርቦት እና ሌሎች ቴክኒካል ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል ያሉት አቶ ጀማል፤ ሚድሮክ ከእርሻ መሬቱ በ20 ኪሎ ሜትር ክልል ውስጥ ሰባት ግዙፍ የሻይ ቅጠል ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ሊገነባ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዚህም ቢያንስ ከ40 ሺህ በላይ ሻይ ቅጠል አምራቾችን ማፍራት እንደሚቻል መናገራቸውን የዘገበው ኢፕድ ነው ።
