ዓለም አቀፉ የክሪፕቶ ምንዛሬ መድረክ የሆነው MEXC የኢትዮጵያ ብርን (ETB) ከP2P ሥርዓቱ ላይ ሙሉ በሙሉ በድንገት ማስወገዱ ተረጋገጠ።
ኩባንያው ቀደም ሲል ይህን አገልግሎት የሚያቆመው እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 ቀን 2026 መሆኑን ገልጾ የነበረ ቢሆንም ከተቀመጠው ቀነ-ገደብ ሃያ ቀናት ቀድሞ ውሳኔውን በተግባር አውሏል። በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ብር ምርጫ ከፕላትፎርሙ ላይ ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል።
ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያን የፋይናንስ ህግ መሰረት አድርገው ፦
– ቴሌግራም ዋሌት
– ቢትጌት
– ባይናንስ
– ኦኬኤክስ
– ባይቢት … የመሳሳሉ መድረኮች በኢትዮጵያን ብር የሚደረጉ የክሪፕቶ ግብይቶች (P2P) ማቆማቸው ይታወሳል።
ብሔራዊ ባንክ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ሥርዓት ያለው የዲጂታል ፋይናንስ ተሳትፎ እንዲኖር የሚያስችል አጠቃላይ የቁጥጥር ማዕቀፍ ለማዘጋጀት ከዓለም አቀፍ አቻ ተቆጣጣሪዎችና ከአገር ውስጥ ባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ መሆኑን መግለጹም ይታወሳል።
@tikvahethiopia
