ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ምግቦች የያዘና ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መዘርዝር (ካታሎግ) እየተዘጋጀ ነው

Date:

ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ምግቦች የያዘ ዓለምአቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መዘርዝር (ካታሎግ) ለሕትመት ለማብቃት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴር ለሕትመት ለማብቃት በዝግጅት ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦች መዘርዝር (ካታሎግ)፤ በተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች የሚዘወተሩ ባህላዊ ሀገራዊ ምግቦችን አዘገጃጀት፣ ይዘት፣ አቀራረብ እና ታሪካዊ ዳራ ያካተተ ስለመሆኑ ለአሐዱ ገልጿል።

በመጽሐፍ መልክ የሚዘጋጀው መዘርዝር ባህላዊ ምግቦችን እንደ “ብራንድ” ወይም ልዩ የቱሪዝም መገለጫ አድርጎ በማስተዋወቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሏል።

የቱሪዝም ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ዓለማየሁ ጌታቸው ይህ ልማድ በሌሎች ሀገራትም እንዳለ አስታውሰው፤ “ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች መረጃዎችን በማሰባሰብ ጥናት በማካሄድ ላይ ይገኛል” ብለዋል።

ኃላፊው እንዳብራሩት፣ ባህላዊ ምግቦችን መለየትና መመዝገቡ መረጃው በአግባቡ እንዲሰነድ፣ በጊዜ ሂደት እንዳይዘነጋጅ፣ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና እንዲያገኝ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል።

ባህላዊ ምግቦታቸውን አጥንተው ለጎብኚዎች በሚመች መንገድ ካዘጋጁ ሀገራት መካከል ጣሊያን፣ ፈረንሳይ፣ ቻይና፣ ሕንድ እና ኮሪያ ተጠቃሽ ናቸው ያለው አሐዱ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...

ኧረ ፋታ ስጡን?!

መንግስት ግን" ምን ሁኑ ?" ሊለን ነው :: አጀንዳ...