ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በልዩ ሁኔታ ለማክበር ያለመውና “ሄር ስቶሪ” የተሰኘው የጋራ የሥነ-ጥበብ ዐውደ ርዕይ፣ ባሳለፍነው ቅዳሜ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በ“ዘ ስፔስ ኢትዮጵያ” ጋለሪ በድምቀት ተከፍቷል።
በታዋቂ እና ተስፋ ሰጪ ሴት ሰዓሊያን ማለትም በአሌክሳንድራ ምትኩ፣ ብሌን ደረሰ፣ ፍቅርተ አያና፣ ምሕረት እሸቱ፣ ኒና ኡርጌሳ፣ ራፋኤላ ፍቃዱ፣ ሩት አስክንድር እና ሩት ጌታቸው የፈጠራ ሥራዎች የተሞላው ይህ ዐውደ ርዕይ፤ ለቀድሞዋ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ መታሰቢያነት የተበረከተ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል።
የሴቶችን ሁነኛ ታሪክና የጥበብ አሻራ በሥዕል የሚተርከው ይህ ዝግጅት፣ እስከ መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለተመልካቾች ክፍት ሆኖ የሚቆይ በመሆኑ፣ የጥበብ አፍቃሪያን ዕድሉን ተጠቅመው እንዲጎበኙ ተጋብዘዋል።
