ለማይቀረው የቻይና ወረራ ዝግጅት እያደረኩ ነው

Date:

የቻይናን  የጥቃት ስልቶችን ለመመከት በሚል በታይዋን ጁላይ 9 በይፋ የጀመረው ዓመታዊ የሃን ኩዋንግ ወታደራዊ ልምምድ የታላቁ ታይፔ አካባቢ ቁልፍ የሆነዉን ድልድይ ሙሉ ለሙሉ መዝጋቱን እና የከተማው ነዋሪዎች ላይ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉ ተሰማ ።

የጠላት ኃይሎች ወደ ታይፔ እንዳይገቡ ለመከላከል የታሰቡ በተባሉት “ግራጫ ቀጠና” የሚል ስያሜ በተሰጠዉ ስልጠናዎች አላማቸዉ የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት ሕንፃ፣ የታይፔ ዋና ጣቢያ እና ሌሎች ቁልፍ ቦታዎች መከላከል የሚያስችሉ እንደሆነ ያሳወቀዉ የታይዋን ጦር የኒው ታይፔ ባንኪያኦ ዲስትሪክት ከታይፔ ዋንዋ ዲስትሪክት ጋር የሚያገናኘው የዋንባን ድልድይ
ልምምዱን ለማቀላጠፍ በሚል ሙሉ ለሙሉ መዘጋቱ ተገልጿል ።

እንደ ታይዋን ትሪቡን የዜና አገልግሎት ዘገባ ከሆነ የቻይና ሃይሎች ወደ ዋና ከተማዋ እንዳይንቀሳቀሱ ለማስቆም ያስችላሉ በተባሉት ልምምዶች ወታደሮች በሁለት ሰአታት ውስጥ በ690 ሜትር ርቀት ላይ ባለ አራት እርከን እገዳን ገንብተዋል ።

ቻይና ከሰሞኑ በታይዋን ዙሪያ የተቀናጀ የጦር ልምምድ ማድረጓን ተከትሎ ታይዋን የወታደራዊ ልምምድ ማድረግ ጀምራለች።

ቻይና ከአሜሪካ ጋር በታይዋን ዙሪያ ወደ ውጊያ ሊገቡ እንደሚችሉ የቻይና ሚዲያዎች ዘግበዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በመንገድ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ...

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...