ለብፁዕ አቡነ አብርሃም በባህርዳር ከተማ አቀባበል ተደረገላቸው

Date:

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሦስት ዓመታት የጠቅላይ ቤተ ክህነት  ዋና ሥራ አስኪያጅነት የአገልግሎት ጊዜያቸውን አጠናቀው ወደ ሀገረ ስብከታቸው መመለሳቸውን ምክንያት በማድረግ በባሕር ዳር  ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ  ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።

በአቀባበሉ ከሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጀምሮ የተለያዩ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን፣ በርካታ ኦርቶዶክሳውያን ተገኝተዋል።

የአቀባበል ሥርዐቱ በባሕር ዳር  ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል መንበረ ጵጵስና የቀጠለ ሲሆን የተለያዩ  መርሐ ግብራትን በማቅረብ  እየተከናወነ ይገኛል።

©ፈለገ ገነት ሚዲያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...

የብሔር ፌደራሊዝምን ለማስቀጠል “የቆረጡ” ተመካካሪዎች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 14ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች የአጀንዳ...

“የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው” ፓትርያርኩ

የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው...