ሊዮኔል ሜሲ እና ሉዊስ ሱዋሬዝ የራሳቸውን የእግር ኳስ ክለብ መመስረታቸውን አስታወቁ። ሁለቱ የልብ ጓደኛሞች ከዚህ በፊት በባርሴሎና አሁን ደግሞ በኢንተር ማያሚ አብረዉ እየተጫወቱ ይገኛሉ።
ዲፖርቲቮ ኤልኤስአም / Deportivo LSM / የተሰኘዉ የሁለቱ ተጫዋቾች የመጀመሪያ ፊደላት ጥምረትን የያዘዉ ቡድን በሱዋሬዝ ሀገር ዪራጓይ ውስጥ የተመሰረተ ነዉ።
ክለቡ በዩራጓይ 4 ኛ ዲቪዚዮን ውስጥ ተሳትፎዉን ሀ ብሎ ይጀምራል የተባለ ሲሆን ቡድን የአዋቂዎች ወይንም የዋና ቡድን እና የወጣት ቡድኖች ይኖሩታል ተብሏል።
ዳጉ ጆርናል
