ሕጉ የወንጀል ምርመራ፣ ክስና ማስረጃ ሥርዓቱን ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ነው

Date:

ከ60 ዓመታት በላይ ያገለገለውን የወንጀል ሥነሥርዓት ሕግ የሚተካ የወንጀል ሥነ ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1410/2018 ሆኖ ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፅደቁን የፍትሕ ሚኒስቴር ገልጿል።

የፍትሕ ሚኒስቴር ፥ ” የ1954 የወንጀል ሥነሥርዓት ሕጉ ለበርካታ አሥርት ዓመታት ሥራ ላይ የቆየ በመሆኑ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግሥት፣ በ1997 ከወጣው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ፣ ሀገራችን ከምትተገብረው የወንጀል ፍትሕ ፖሊሲ እንዲሁም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በዘርፉ ካሉ አዳዲስ አሠራሮችና የቴክኖሎጂ እድገቶች አኳያ ከዘመኑ ጋር በተጣጣመ መልኩ መከለሱ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ባለፉት ዓመታት የአዲስ ሕግ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል ” ብሏል።

ዛሬ የጸደቀው የሕግ መድብል አዳዲስ አሠራሮችን ከማስተዋወቁ በተጨማሪ የማስረጃ ሕግ በማካተት በኢትዮጵያ የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ውስጥ የቆየውን አንድ ትልቅ ክፍተት ለመሙላት እንዳስቻለ ገልጿል።

” ሕጉ የወንጀል ምርመራ ፣ ክስ እና ማስረጃ ሥርዓቱን ወደአዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ነው ” ብሏል።

” የወንጀል ሥነ ሥርዓት እና ማስረጃ ሕጉ በማርቀቅ ሂደት ከ15 ዓመታት በላይ የወሰደ ሲሆን ባለፉት የለውጥ ዓመታት ከተለዩ ቁልፍ የሕግ ሪፎርሞች አንዱ ሆኖ፣ ብዙ ምክክር ተደርጎበት ሊጸድቅ ችሏል ” ሲል አስረድቷል።

ሚኒስቴሩ ” ሕጉ ሀገር አቀፍ ተፈጻሚነት ያለው ሲሆን ከዚህ ሪፎርም የሚጠበቀውን ውጤት እውን ለማድረግ በሁሉም ደረጃ ከሚገኙ የፍትሕ አካላት ጋር በቅንጅት እንሰራለን ” ብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...