መምህሩና አዲስ ተመራቂ ባለቤታቸው በደረሰ አደጋ ሕይወታቸው አለፈ

Date:

​በካፋ ዞን ሺሾ እንዴ ወረዳ በደረሰ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ፣ የአንድ መምህርና ገና ዛሬ ከኮሌጅ የተመረቀች ባለቤታቸው ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ማለፉ ተሰማ። ሕ

ይወታቸው ያለፈው መምህር አብሪሃም ግዛው እና ባለቤቱ መምህርት ራሄል አክሊ መሆናቸው ታውቋል።

​አደጋው የደረሰው ዛሬ  ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 5:30 ገደማ፣ ከቦንጋ ወደ ሺሺንዳ በመጓዝ ላይ በነበረና የሰሌዳ ቁጥሩ 00582 በሆነ የ”ዶልፊን” የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ ነው።

መኪናው ዋና ቦላ በተባለ ቀበሌ ላይ መንገድ ስቶ 50 ሜትር ገደል ውስጥ በመግባቱ ጥንዶቹ ወዲያውኑ ሕይወታቸው አልፏል።

መምህርት ራሄል የኮሌጅ ምረቃዋን አጠናቃ በደስታ ወደ ቤት እየተመለሰች ነበር።

​በአደጋው ሌሎች ተሳፋሪዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን፣ በዲንቢራ ጤና ጣቢያ የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዜጋዬ ተገድሏል ያለችው ጋና ከደቡብ አፍሪካ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ውስጥ ገባች

አንድ ጋናዊ በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ካለው ፀረ ስደተኞች ተቃውሞ...

«የማይናገረው ልዑል» መጽሐፍ በታላቅ ድምቀት ሊመረቅ ነው

ደራሲ መሠረት ክንፈ ኃይሌ ከኦቲዝም ጋር ከሚኖረው ልጇ ልዑል...

በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር የሚደረግ ንግድ በገንዘብ መጠን ተገደበ

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር የሚከናወነውን...

(IMF) ከ460 ሚሊዮን ዶላር በላይ ብድር አፀደቀ

አዳዲስ ብድር በመውሰድ ረገድ ጥንቃቄ እንድታደርግ ኢትዮጵያን ያስጠነቀቀው IMF...