መስከረም ጌታቸው መልቲሚዲያ ወደ 3 ወር የወሰደ የሚዲያ ስልጠና ሲሰጥ ቆይቶ መስከረም 18 ቀን 2018 ዓ.ም 45 ሰልጣኞችን በግራንድ ኤልያና ሆቴል አስመርቋል።
በእውቅና ፕሮግራሙ የክብር እንግዳ የሆኑት አቶ አማረ አረጋዊ የኢትዮጵያ ሚዲያ ካውንስል ሰብሳቢና የሪፖርተር ጋዜጣ ባለቤት ናቸው። አንጋፋው ባለሙያ አቶ አማረ ለሰልጣኞቻችን የሚዲያን አስፈላጊነትና አጠቃቀም ላይ መልእክት በማስተላለፍ ባለሙያዎችን በማብቃት ላይ ከተቋማችን ጋር ለመስራት ቃል ገብተዋል።
አቶ አድማሱ ዳምጠው የፋና ሚዲያ ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተገኝተው ለተማሪዎቻችን የእውቅና ሰርተፍኬት ከመስጠት ባለፈ መልእክት አስተላልፈው ተቋማችንን እና ሰልጣኞችን እንደሚያግዙ ገልጸዋል።
ሌሎች የጋበዝናቸው ሐውለት አህመድ(የአአዩ መምሀርት እና የንግድ ሥራ አማካሪ) ሚዲያና ቢዝነስ በሚል ጉዳይ የመቅዶንያ መስራች አቶ ብንያም በለጠ ሚዲያን ለበጎ ሥራ በሚል ጉዳይ ሃሳባቸውን አጋርተውናል።
ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ ለዕለቱ ልዩ እውቅና ለሰጠናቸው ከ9-12 ጂኦግራፊ ላስተማሩኝ እና እንደልጃቸው ለሚያበርቱኝ መመህሬ ለአቶ ወርቁ አሸናፊ ያዘጋጀሁትን የክብር ካባ በማልበስ የልቤን ሞልተውኛል።
በርካታ የሚዲያ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ በተለያየ ሙያ ያሉ ተጋባዦች እና ተመራቂዎች የመርሐ ግብሩ ድምቀት ነበሩ።
ከሰልጣኞች ከ1-3 ለወጡ፣ ለተጋባዥ መምህራን፣ ለተግባራዊ ጉብኝት ፍቃደኛ የሆኑትን ፋና እና ኢቲቪን እውቅና ሰጥተናል።
በስልጠናው በአካል እና በኦንላይን የተሰጠ ሲሆን ከአሜሪካ፣ ካናዳ፣ እስራኤል፣ ዱባይ ከሀገር ውስጥ ወላይታ ባሕር ዳር ተሳትፈዋል።
የትምህርት አይነቶችም ዜና እና ዲጂታል ሚዲያ፣ ዘጋቢ ፊልም እና ቃለ መጠይቅ ናቸው።
ሰልጣኞቻችን 98% የሚሆኑት የመጀመሪያ ዲግሪ እና ሁለተኛ ዲግሪ በተፈጥሮ ሳይንስና ማኅበራዊ ሳይንስ ያላቸው ነገር ግን የጋዜጠኝነት ፍቅር እያላቸው በሌላ ትምህርት መስክ የተመረቁ ናቸው።
ሁለተኛ ዙር ምዝገባ ላይ ስንሆን ጥቅምት ላይ ትምህርቱ ይጀመራል።
