“መደመር ትውልድን ወደ ብልፅግና የሚያደርስ መንገድ ነው”

Date:


የአመራር ቁርጠኝነት፣ በፈጠራ፣ በፍጥነትና በጥራት መስራት ለሁለንተናዊ ብልፅግና መረጋገጥ አስፈላጊ እንደሆነ የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዝዳንትና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለፁ።

የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዝዳንትና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግሥት ማጠቃለያ ስልጠና ላይ እንደገለፁት የአመራሩ ቁርጠኝነት፣ በፈጠራ፣ በፍጥነትና በጥራት መስራት ለሁለንተናዊ ብልፅግና መረጋገጥ አስፈላጊ ነው።

ትኩረት የሚሹ ግቦችን በየፈርጁ በመለየት አቅጣጫ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ፋይዳ መታወቂያ፣ 5 ሚሊዮን ኮደሮች፣ የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች፣ የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች፣ የምርጫ ምቹነትና የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም አጀንዳዎች በ100 ፕርሰንት ለማሳካት መትጋት የሚገባን ግቦች ናቸው ብለዋል።

የመደመር መንግሥት ለሀገር ብልፅግና ባለአደራ መሆኑንም ተናግረው በፈጠራና በፍጥነት ጥራትና ብዛትን እውን ማድረግ ይገባል። በብዝሀ ዘርፍ ትስስር ወደ ስልጣኔ ሽግግር ማምጣት ይገባል ብለዋል።

ሁሉም የፓርቲው አመራር በዚህ አግባብ በመትጋት ሁለንተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥ አለበት ብለዋል።

በስልጠናው የመደመር መንግሥት ፅንሰ ሀሳብ፣ መንገድና መዳረሻ ግቦቹ የተዳሰሱ ሲሆን አመራሮች በፈጠራ በፍጥነት በብዛት ስራዎችን በማከናወን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ በሚረዳ መንገድ መምራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

“በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እምርታ” በሚል ለፌደራል፣ ለክልል፣ ለከተማ አስተዳደርና ከፍተኛ አመራሮች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል።

ጋዜጣ ፕላስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...