ለበርካታ ህጻናት ህይወት መቀየር ምክንያት መሆኑን ያነሳው ሰአሊ ብሩክ የሺጥላ በተሰጠው ሀላፊነት ደስተኛ መሆኑንና የተጣለበትን አደራ ለመወጣት እንደሚሰራ ተናግሯል።
በዝግጅቱም ብሩክ ለብርሃን ህጻናት ግብረ ሰናይ ድርጅት በቀለማት ህብር ያሸበረቀ የስዕል ሥራውን በስጦታ አበርክቷል።
ድርጅቱ አካል ጉዳተኛ ህጻናትን እንዲሁም ልጃገረዶችና ቤተሰቦቻቸውን ተደራሽ የሚያደርጉ ድጋፎችን በማቅረብ የሚሰራ እንደሆነም ተገልጿል።
በተለይ በኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋር፣ ሲዳማ ክልሎች እና መካከለኛው ኢትዮጵያ ለ30 አመታት ሲሰራ ቆይቷል።
በXነዚህ ጊዜያት ከ23 ሺህ በላይ ህጻናትን ሲያግዝ እንደነበረም ተጠቁሟል።
በተጨማሪም የግጭት አፈታትና የሰላም ግንባታ፣ ኤች አይ ቪ ኤድስን መከላከል፣ የስርዓተ ፆታ ማካተት እና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ማስወገድ ላይ ይሰራል።
ድርጅቱ ዩኒሴፍ፣ ላይት ፎር ዘ ወርልድ ከተሰኙ እና ሌሎች አጋር አካላት የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚደረግለት ተገልጿል።
