ሃይንከን በአልኮል መጠኑ ጠንከር ያለ ቢራ ለኢትዮጵያ ገበያ አስተዋወቀ

Date:

ሃይንከን ኢትዮጵያ በእለም አቀፍ ደረጃ ዝነኛ የሆነውን ዴሰፔራዶስ (Desperados) የተሰኘ ቢራ ለኢትዮጵያ ገበያ አስተዋወቀ።

ሃይንከን ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ተወዳጅነቱ የሚታወቀውንና በልዩ ጣዕም የተጠመቀውን ዴስፔራዶስ (Desperados) ቢራ ዛሬ ሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ለኢትዮጵያ ገበያ እስተዋውቋል። የዚህ ዓለም አቀፍ ብራንድ መምጣት በሀገሪቱ የፕሪሚየም ቢራ ገበያ ላይ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ሲሆን፤ ለዘርፉ ዕድገትም የላቀ እስተዋጽኦ ይኖረዋል።

ከሦሰት እሰርት ዓመታት በላይ የዘለቀ ታሪክ ያለውና ከ50 በላይ በሚሆኑ ሀገራት የሚገኘው ዴስፔራዶስ፤ የቢራ ጠመቃ ጥበብን ከልዩ ጣዕም ጋር በማዋሃድ አዲስ የቢራ ተሞክሮን ለአለም ማስተዋወቁን ሃይንከን ኢትዮጵያ ገልጷል።

እንደኩባንያው ገለጻ ዴሰፔራዶስ ከቢራም በላይ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ የነጭ እልኮል መጠጦች (Spirits) ዋነኛ ግብዓት በሆነው በአጋቬ (Agave) ጣዕም የተጠመቀ ፈር ቀዳጅ ቢራ ሲሆነ፣ በ 5 ነጥብ 9 በመቶ የአልኮል መጠኑ በቢራ እና በጠንካራ አልኮል መጠጦች መካከል አዲስ የጣዕም ድልድይ ፈጥሯል።

የወጣቶች የመዝናኛ ዘይቤ እየተለዋወጠ እና አዲስ ነገርን የመፈለግ ዝንባሌ እየጨመረ በመጣበት በዚህ ወቅት የምርቱ ለገበያ መቅረብ፤ ሃይንከን ኢትዮጵያ የተጠቃሚዎችን ፍላጎት ለሟሟላት ያለውን ስትራቴጂካዊ ቁርጠኝነት በተግባር ያሳያል፡፡

ለየት ያለ አማራጭ ለሚሹ እና ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤን ለሚከተሉ ወጣቶች ተስማሚ ሆና የተዘጋጀው ዴስፔራዶስ፤ ከአዳዲሰ የሙዚቃ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር እንደአቬኒዳ ዴስፔራዶስ (Avenida Desperados) ያሉ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ለተጠቃሚዎቹ ያስተዋውቃል፡፡

ሃይንከን ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያተረፈ ብራንድ በሀገር ውስጥ ማምረት መጀመሩ፣ በኢትዮጵያ ያለውን የረዥም ጊዜ ቁርጠኝነት እና በሀገሪቱ የገበያ እድገት ላይ ያለውን ጽኑ እምነት በድጋሚ አረጋግጧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...