ለኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ የሚውል የ40 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ተፈቀደ

Date:

የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የልማት ክንፍ የሆነው ኢአይቢ ግሎባል (EIB Global)  እና ዘመን  ባንክ  በኢትዮጵያ ለሚገኙ የግብርና ኤክስፖርት ድርጅቶች የሚውል የ40 ሚሊዮን ዩሮ የፋይናንስ  ስምምነት መፈራረማቸውን  አስታወቁ። 


በአዲስ አበባ በተካሄደው  የአውሮፓ ህብረት-ኢትዮጵያ  የንግድ ፎረም ላይ ይፋ በሆነው በዚህ ስምምነት መሠረት ኢአይቢ ግሎባል (EIB Global) 20 ሚሊዮን  ዩሮ  ብድር  ለዘመን  ባንክ አቅርቡዋል ዘመን  ባንክ በበኩሉ ተጨማሪ 20 ሚሊዮን  ዩሮ በመመደብ  ጠቅላላ የገንዘብ መጠኑን 40 ሚሊዮን  ዩሮ  አድርሶታል ። 

ይህ ብድር  ኢአይቢ ግሎባል (EIB Global)  በኢትዮጵያ  ለሚገኝ የንግድ ባንክ በቀጥታ የሰጠው የመጀመሪያው ብድር ነው። 

የገንዘብ ድጋፉ  በዋናነት  በግብርናው  ዘርፍ ለተሰማሩና  ምርቶቻቸውን  ወደ  ውጭ ለሚልኩ አነስተኛና  መካከለኛ  ኢንተርፕራይዞች (SMEs) የሚውል ሲሆን በተለይም ቡና እንዲሁም  የአትክልትና  ፍራፍሬ (Horticulture) ላኪዎችን ይደግፋል ፤ በተጨማሪም  30 በመቶ  የሚሆነው  የገንዘብ ድጋፍ  ለአካባቢ  ጥበቃ  እና  ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም ለሚሰሩ ድርጅቶች እንደሚውል ተጠቁሙዋል፡፡

ከተገኘው ገንዘብ ውስጥ ቢያንስ 30 በመቶ የሚሆነው የገንዘብ ድጋፍ በሴቶች ለሚመሩ ወይም ለሴቶች የሥራ ዕድል ለሚፈጥሩ ድርጅቶች እንዲውልም ተወስኗል። 

ስምምነቱ  ዛሬ በአዲስ አበባ በተካሄደው እና በአውሮፓ ህብረት የዓለም አቀፍግንኙነት ኮሚሽነር ጆዜፍ ሲኬላ እንዲሁም በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙነት የአውሮፓ ህብረት-ኢትዮጵያ የንግድ ፎረም ላይ ይፋ ሆኗል።

የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት አምብሮይስ  ፋዮል እንደገለጹት ግብርና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት በመሆኑ ይህ የብድር መስመር የግል ካፒታልን ወደ ግብርናው ዘርፍ ለማፍሰስ እንደ ማነቃቂያ ያገለግላል።

የዘመን ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ደረጄ ዘበነ በበኩላቸው ዘይህ አጋርነት የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ አርሶ አደሮችን ለማብቃት እና ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገትን ለማምጣት ያለንን ቁርጠኝነት ያሳያል” ብለዋል።

በተጨማሪም ዘመን  ባንክ ከዚህ የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ፣ የአየር ንብረት ለውጥን  መቋቋም የሚችሉ የፋይናንስ ሥርዓቶችን ለመገንባት እንዲረዳው ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የቴክኒክ ድጋፍ በማግኘት ላይ እንደሚገን ተገልፁዋል ። 

ግብርና ከኢትዮጵያ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ውስጥ ከአንድ ሶስተኛ በላይ የሚሆነውን ድርሻ ይይዛል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...

ከ 50 ሚሊዮን በላይ መራጮች በማንዋልና በዲጂታል ተመዝግበዋል

ከየካቲት 28_መጋቢት 28 የመራጮች ምዝገባ ሲካሄድ እንደነበር ይታወቃል። በተለያዩ ጉዳዮች...

በኦሮሚያ ክልል የ4.5 ሚሊዮን ዶላር የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

ፈያ ኢንተግሬትድ ዴቬሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን በኦሮሚያ ክልል የሚከሰቱ የበሽታ ወረርሽኞችን...