ሲፒጄ በሽብርተኝነት የተከሰሱ አራት ጋዜጠኞች ፍትሐዊ እና ግልጽ የፍርድ ሂደት እንዲያገኙ አሳሰበ

Date:

የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲፒጄ)፣ በሽብርተኝነት ወንጀል የተከሰሱ አራት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ፍትሐዊ፣ ግልጽ እና ሕጋዊ ሥርዓቱን የጠበቀ የፍርድ ሂደት እንዲያገኙ አሳሰበ።

ድርጅቱ የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፣ መስከረም አበራ፣ ገነት አስማማው እና ዳዊት በጋሻው አስፈላጊው የሕግ ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ አሳስቧል።

ድርጅቱ እነዚህ ጋዜጠኞች በአማራ ክልል ከነበረው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ በሰሩት ዘገባዎች ምክንያት በቁጥጥር ስር ውለው ላለፉት ሦስት ዓመታት ገደማ በእስር ላይ ይገኛሉ ብሏል።

ከእነዚህ መካከል “የአማራ ድምፅ” ሚዲያ መስራች ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፣ እ.ኤ.አ ግንቦት 2023 በጅቡቲ በቁጥጥር ስር ውሎ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፎ መሰጠቱ ይታወሳል ሲል አክሏል።

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቅርቡ በሰጠው ብይን፣ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበው ማስረጃ ተከሳሾቹን ለመከላከል የሚያበቃ ነው በማለቱ፣ ጋዜጠኞቹ በመጪው ግንቦት ወር መከላከያቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የ“ኢትዮ ንቃት” ሚዲያ መሥራች እና አዘጋጅ መስከረም አበራ፣ የ“የኛ” ሚዲያ ሪፖርተር ገነት አስማማው እና የ“አራት ኪሎ” ሚዲያ አዘጋጅ ዳዊት በጋሻው ከሌሎች አምስት ጋዜጠኞች ጋር በመሆን እ.ኤ.አ በሚያዝያ 2023 መጀመሪያ ላይ መታሰራቸው ይታወሳል።

ሲፒጄ በመግለጫው፣ ጋዜጠኞቹ ለረጅም ጊዜ በእስር መቆየታቸው እና የቀረበባቸው ክስ ክብደት በኢትዮጵያ ያለውን የፕሬስ ነፃነትን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን ገልጿል። በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግስት ዓለም አቀፍ የፍትሐዊ የፍርድ ሂደት መስፈርቶችን እንዲያከብው ጥሪ አቅርቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...