ሳፋሪኮም ከስታንዳርድ ባንክ ለዲጂታል ማስፋፊያ የ138 ሚሊዮን ዶላር አገኝ

Date:

ሳፋሪኮም ቴሌኮሙኒኬሽን ኢትዮጵያ በአፍሪካ ግዙፉ ባንክ ከሆነው ከስታንዳርድ ባንክ የ138 ሚሊዮን ዶላር (R2.4 ቢሊዮን) የገንዘብ ድጋፍ ማግኘቱ ተገለጸ። ይህ ፋይናንስ ኩባንያው በኢትዮጵያ እያካሄደ ያለውን የዲጂታል መሠረተ ልማትና አገልግሎት ማስፋፊያ ሥራ ለማገዝ ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

ስታንዳርድ ባንክ ለ ሳፋሪኮም የተሰጠው የብድር ፋሲሊቲ ብቸኛ አደራጅ፣ አበዳሪና ፋሲሊቲ ወኪል ሆኖ እንዲሁም የአማካሪነት ሚና መጫወቱን በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

ይህ ድጋፍ በኬንያ ትልቁ የቴሌኮሙኒኬሽን አቅራቢ የሆነው ሰፋሪኮም በኢትዮጵያ የቴሌኮም ገበያ ውስጥ ያለውን ተሳትፎ የበለጠ ለማጠናከር ያስችለዋል።

የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያው በ2021 በኢትዮጵያ ውስጥ ለመሥራት ፈቃድ ያገኘ ሲሆን ስታንዳርድ ባንክ በአገሪቱ አገልግሎት ሲሰጥ እና አውታረ መረብ ሲዘረጋ አብረው ከሰሩት አማካሪዎችና ፋይናንስ አቅራቢዎች አንዱ እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በአዲስ አበባ የታክስ ዕዳ ምህረት አሰጣጥን የሚያስተዳድር አዲስ ረቂቅ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ፣ በተለያዩ ከግብር ከፋዮች...

እግዚአብሔር የሰጠኝን ተልዕኮዎች ፈጽሜያለሁ የአዛዥነት ዘመኔ እያበቃ ነው

የኡጋንዳ የመከላከያ ኃይሎች አዛዥ (CDF) ጄነራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ ከወታደራዊ...

አሐዱ ባንክ 1ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር አተረፈ

ባንኩ በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር...

በጋምቤላ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ነዋሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከለ

ከጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው ጋምቤላ...