የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የካፍ ይግባኝ ሰሚ ቦርድ ከሴኔጋል ነጥቆ የአፍሪካ ዋንጫውን ለሞሮኮ ብሄራዊ ቡድን መስጠቱን አሳዉቋል።
የካፍ ይግባኝ ሰሚ ቦርድ የ 2025 ቱን የሴኔጋልና ሞሮኮ የፍጻሜ ጨዋታን ዉጤት በመሻር የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለካፍ ያስገባዉን ይግባኝ ተከትሎ ሞሮኮ የ 2025 የአፍሪካ አሸናፊ መሆኗን ይፋ አደርጓል።
የካፍ ይግባኝ ሰሚ ቦርድ FRMF ከሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቀረበልንን የቅሬታ ደብዳቤ ተመልክተናል በዚህ መሠረት የሞሮኮ ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል ይህ ታሪካዊ ዉሳኔ ነዉ የክርክሩ መነሻ የሴኔጋል አሰልጣኝ ፓፔ ቲያዉ ተጫዋቾቹ ሜዳዉን ለቀዉ እንዲወጡ አድርገዋል በማለት ያስታወሰዉ የካፍ ይግባኝ ቦርድ ተከታዮን ሀሳብ አጋርቷል:-
ውሳኔው የመጣው የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይግባኝ ካቀረበ በኋላ እንደሆነ በመግለፅ ውሳኔው በመዘግየቱ ይቅርታ እንጠይቃለን ብለዋል ለሞሮኮ እንኳን ደስ አላችሁ ካሉ በኋላ ሴኔጋልን ደግሞ ሌላ ተጨማሪ ቅጣት እንደሚጠብቃት የካፍ ይግባኝ ሰሚ ቦርድ ገልጿል።
የሴኔጋል ተጫዋቾች በሜዳ ላይ ያሳዮት ባህሪ በአፍሪካ ዋንጫ ደንብ አንቀጽ 82 እና 84 መሠረት የሴኔጋል ተጫዋቾች ከሜዳ መዉጣታቸዉ ህጉን መጣሱን ያሳያል ከዚህ በፊት የካፍ የዲስፕሊን ቦርድ ዉሳኔን ወደ ጎን በመተዉ የሞሮኮ ጥያቄን ተቀብለን አጽድቀናል በማለት የካፍ ይግባኝ ቦርድ ዉሳኔዉን አሳዉቀዋል።
የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ውጤት ተሽሯል ስለዚህ ሞሮኮ በፎርፌ የአፍሪካ ዋንጫው አሸናፊ እንድትሆን የካፍ ይግባኝ ሰሚ ቦርድ ወስኗል። ሴኔጋል በፎርፌ 3-0 ተሸንፋ ዋንጫው ለሞሮኮ እንዲሰጥ መወሰኑ ብዙዎችን እያነጋገረ ይገኛል። #የሴኔጋል ሰዎች ጉዳዮን ወደ ካፍ ለመዉሰድ እንቅስቃሴ ጀምረዋል።
