ሶማሊያ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጋር የነበራትን ስምምነቶች በሙሉ አቋረጠች

Date:

የሶማሊያ መንግሥት ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጋር የተደረጉ የወደብ እና የደህንነት ትብብርን ጨምሮ ሁሉንም ስምምነቶች ማቋረጡን አስታውቋል ።

ይህ ውሳኔ የተላለፈው ሉዓላዊነትን፣ የግዛት አንድነትን እና የአገሪቱን የፖለቲካ ነፃነት የሚነኩ የጥላቻ ድርጊቶችን የሚመለከቱ አሳማኝ ማስረጃዎች መሰረት በማድረግ ነው ።

ውሳኔው በርበራን ጨምሮ ከወደቦች ጋር የተያያዙ ሁሉም ስምምነቶች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል ። በተጨማሪም የሁለትዮሽ የደህንነት እና የመከላከያ ትብብር ስምምነቶች ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆን ተገልጿል ።

የሶማሊያ መንግስት በዚህ ወቅት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም እያዳከመች ነው ሲል መክሰሱን ሮይተርስ ዘግቧል ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...