በመቐለ ከተማ በአንድ ሌሊት ሦስት ሰዎች ባልታወቁ ዘራፊዎች ተገድለዋል

Date:

           

ግድያዎቹ ነሀሴ 9/2017 ዓ.ም ሌሊት ሰሜን ፣ ቀዳማይ ወያነና ሓድነት በተባሉ ክፍለ ከተሞች መፈፀማቸው የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል አረጋግጧል።

በአሰቃቂ ግድያው የሁለት ወንድና አንድ ሴት ህይወት ተቀጥፈዋል።

ነሀሴ 6/2017 ዓ.ም እንዲሁ በመቐለና አክሱም ከተሞች ሁለት ሰዎች ማንነታቸው ባልታወቁ ዘራፊዎች ተገድለዋል።

ነሀሴ 4/2017 ዓ.ም ሌሊት በከተማዋ ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች ታግቶ የተሰወረው የፊልም ባለሙያም እስከ አሁን አልተገኘም።

የሰላማውያን ሰዎች እገታና ግድያ ተባብሶ መቀጠሉ የሚቀበለው የፀጥታ አካል ችግሩ ለመፍታትና ለመቆጣጠር የህዝቡ ትብብርና ተሳትፎ ጠይቋል።

የመቐለ ከተማ የፀጥታ ዘርፍ ነሀሴ 10/2017 ዓ.ም በጠራው የህዝብ ውይይት የተገኙት የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ ረደሀኝ ፍሰሃ ከጦርነቱ በኃላ በከተማዋ የተፈጠረው የፀጥታ ችግር ጤናማ ለማድረግ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ መደረጋቸው በማውሳት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ችግሩ መልሶ ማገርሸቱ ገልፀዋል።

በአይነትና የአፈፃፀም ስልታቸው የተለዩና ያልተለመዱ ፦

  • የተደራጀ ቅምያና እገታ ፣
  • ህገወጥ የሰዎችና የትጥቅ ዝውውር ፣
  • የሴቶች ጥቃት
  • የመሬት ወረራ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር እጦት መኖራቸው የሚቀበሉት ኃላፊው ማህበራዊ ሚድያው እነዚሁ በማባባስ አሉታዊ ሚና እየተጫወተ ነው ብለዋል።

” ችግሮቹ ከህዝብና የፀጥታ አካላት አቅም በላይ አይደሉም ” የሚሉት ኃላፊው ” ህዝቡ የፀጥታ አካሉ ተቀናጅተው መንቀሳቀስ ከቻሉ በአጭር ጊዜ አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ ይቻላል ” ሲሉ ገልጸዋል።

የውይይቱ ተሳታፊ የሆኑት የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ጌታቸው ኪሮስ ፥ የፀጥታ ችግሩ ከመቐለ ባሻገር በመላ የክልሉ አካባቢዎች እንደሚታይ በመግለፅ ” የችግሩ ዋና መፍትሄ ህዝቡ ከላይ እከታች በማደራጀት የፀጥታው ባለቤት እንዲሆን ማስቻል ነው ” ብለዋል።

ከቀናት በፊት የዘንድሮ የአሸንዳ በዓል አከባበር አስመልክቶ ከባለ ድርሻ አካላት ውይይት ተካሂዶ ነበር። በወቅቱ የተገኙት ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል ) በዓሉ በተረጋጋ ሁኔታ እንዲከበር በተለይ ደግሞ የሚታዩት ከባባድ ወንጀሎች ለመቆጣጠር የሚያስችል እንቅስቃሴ በመመከናወን ላይ እንደሆነ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...