በሮቦቶች ብቻ የሚተዳደር የአለማችንን የመጀመርያውን ሆቴል

Date:

ቻይና በፈረንጆቹ 2027 ሙሉ በሙሉ በሮቦቶች ብቻ የሚተዳደረውን የዓለማችንን የመጀመሪያውን ሆቴል በጓንግዶንግ ግዛት ለመክፈት አቅዳለች።

የዚህ ታሪካዊ ፕሮጀክት የሙከራ ትዕይንት በ2026 መገባደጃ ላይ የሚጀመር ይሆናል።

በታዋቂው “ፑዱ ሮቦቲክስ” ኩባንያ የሚገነባው ይህ ሆቴል፤ ለእንግዶች መስተንግዶ፣ ለክፍል አገልግሎት፣ ለጽዳት፣ ለምግብ ዝግጅት፣ ለሻንጣ ማጓጓዝ እንዲሁም ለአጠቃላይ የእንግዳ መስተንግዶ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የታጠቁ ሮቦቶችን በስራ ላይ ያሰማራል።

ይህንን ዘመናዊ አገልግሎት ልዩ የሚያደርገው በርካታ ሮቦቶች “PuduFM 1.0” እና “PuduAgent” በተባሉ የቴክኖሎጂ ሲስተሞች አማካኝነት እርስ በርስ መገናኘት መቻላቸው ነው።

ይህም ሮቦቶቹ መረጃዎችን እንዲለዋወጡና በመላው ሆቴሉ ውስጥ የሚከናወኑ ተግባራትን በቅንጅት እንዲመሩ ያስችላቸዋል።

ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በ”ሼንዘን የባህል እና ቱሪዝም ኢንዱስትሪ ልማት” እና በ”ሼንዘን-ዦንግሻን ሊንክ” ምዕራባዊ ሰው ሰራሽ ደሴት ልማት ትብብር የሚከናወን ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...

አዲስ አበባ፦ የዜጎች ቀይ መስመር!

(የግል አስተያየት) አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መናገሻ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች ለዘመናት...

አብን የምክክሩን ውጤት ውድቅ አደረገ!

አብን በሀገራዊ ምክክሩ ማጠቃለያ ላይ የተፈጸመውን “ሕገ-ወጥ ጣልቃ-ገብነት” በመቃወም...