በሳውዲ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ የውጪ ዜጎች በሞት ተቀጡ

Date:

በሳውዲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ የውጪ ዜጎች በአድንዛዥ እፅ ምክንያት የሚፈጸም የሞት ቅጣት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን አምነስቲ በሪፖርቱ ላይ ገልጿል።

ሳዑዲ አረቢያ ባለፈው ዓመት 345 ሰዎችን በሞት የቀጣች ሲሆን፣ ይህም አምነስቲ ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ከመዘገበው ከፍተኛው ቁጥር ነው ብሏል።

ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ 180 ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል ያለው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኑ፣ ይህም ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል አመልክቷል።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከጥር 2014 እስከ ሰኔ 2025 ባለው ጊዜ ውስጥ ሳዑዲ አረቢያ 1,816 ሰዎችን በሞት መቅጣቷን የአገሪቱ የፕሬስ ኤጀንሲ አስታውቋል።

በሰኔ 2025 ብቻ አገሪቱ 46 ሰዎችን በሞት የቀጣች ሲሆን 37ቱ ከአደንዛዥ ዕፅ ጋር በተያያዘ ሲሆን ይህ ማለት ከአደንዛዥ ዕጽ ጋር በተያያዘ በቀን በአማካይ ከአንድ ሰው በላይ በሞት ይቀጣል ማለት እንደሆነ አምነስቲ በሪፖርቱ ላይ አመልክቷል ሲል ቢቢሲ በዘገባው አስፍሮታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የዓለም የቡና ገበያ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተገለጠ

በዓለም አቀፍ ደረጃ በቡና አቅርቦት ላይ ተፈጥሮ የነበረው ስጋት...

አሜሪካ የኢራንን የጭነት መርከብን መያዟን አስታወቀች

በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን የዘጋችው...

“ቴዲ አፍሮ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ቀይሮታል!” — ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

በ"ወቸው ጉድ" ፖድካስት ላይ እንግዳ ሆነው የቀረቡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ...