በባንግላዲሽ ዋና ከተማ ዳካ የአየር ኃይል ማሰልጠኛ ጄት አውሮፕላን ተከስክሶ ቢያንስ 19 ሰዎች ሲሞቱ 164 ሰዎች ቆስለዋል።
አደጋው የደረሰው የF-7 BGI የተሰኘ የአየር ሀይል ጄት ለልምምድ በተነሳ በጥቂት ደቂቃ ውስጥ በዳካ በሚገኝ ትምህርት ቤት ጊቢ የተከሰከሰ ሲሆን ቢያንስ 19 ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል ።
ከሟቾቹ መካከልም የአውሮፕላኑ አብራሪ እና በርካታ ተማሪዎች ይገኙበታል የተባለው ሲሆን በአደጋው ሰለባ የሆኑ ተማሪዎች
እድሜያቸው ከአራት እስከ 18 ዓመት መካከል እንደሆነ ተገልጿል ።
የአየር ኃይል ጀቱ ሚልስተን ኮሌጅ እና ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ሲለሰከስ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ውስጥ እንደነበሩ ተዘግቧል።
ከባንግላዲሽ አየር ኃይል ኩርሚቶላ ቤዝ ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ምክንያት አውሮፕላኑ ሊከሰከስ እንደቻለ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ሌተና ኮሎኔል ሳሚ ኡድ ዶውላ ቾውዱሪ ተናግረዋል። ዘገባው የሮይተርስ ነው
NBC Ethiopia
