በአለም ከመጠን በላይ የወፈሩ ሰዎች አንድ ቢልየን አልፏል

Date:

በዓለም አቀፍ ደረጃ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያላቸው ሰዎች ቁጥር ከአንድ ቢሊዮን በላይ መድረሱን ዘ ላንሴት በተባለ ሳይንሳዊ መጽሔት ላይ የወጣ አንድ ጥናት አመለከተ።

ትንታኔው በፈረንጆቹ 1990 እስከ 2022 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ190 በሚበልጡ አገሮች የተገኘውን መረጃ ያካተተ ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ከመጠን ያለፈ ውፍረት በልጆችና በአዋቂዎች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።
ይህም በሴት ልጆች ከ1.7% ወደ 6.9% እንዲሁም በወንድ ልጆች ከ2.1% ወደ 9.3% ከፍ ብሏል።

እ.ኤ.አ. በ2022 ወደ 160 ሚሊዮን የሚጠጉ ታዳጊዎች ከመጠን በላይ  ውፍረው ነበረ።

በአዋቂዎችም ዘንድ ችግሩ ተባብሷል። ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያለባቸው ሴቶች መጠን ከ 8.8% ወደ 18.5% ሲጨምር፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያለባቸው ወንዶች መጠን ደግሞ ከ 4.8% ወደ 14% ከፍ ብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...

ሕወሓት ድብረጺዮንን የክልሉ ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ

የክልሉ ፕሬዚዳንት ተደርገው የተመረጡት  ድብርጺዮን ገ/ ሚካዔል (ዶ/ር)  ቃለ...

” ኢራን ከምድረ ገጽ ትጠፋለች ” – ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ቴሌቪዥን ጋር ቃለ...

የአርበኞች ድል መታሰቢያ እና የዛሬው ትውልድ ለሕብረት ያለው አቋም

የጥንት ኢትዮጵያዊያንአርበኞች ድል 85 ኛው ዓመት መታሰቢያ ሚያዚያ...