በአማራ ክልል በርካታ የደረጃ “ሀ” ግብር ከፋዮች ግብራቸውን አላሳወቁም

Date:

​አማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት ውስጥ ከ16 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ቢሰበስብም፣ አብዛኛዎቹ የደረጃ “ሀ” ግብር ከፋዮች ግብራቸውን ባለማሳወቃቸው በቀሪ ጊዜያት እንዲከፍሉ አስጠነቀቀ።

​የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ የግብር ትምህርት እና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ታዘባቸው ጣሴ ፤ ቢሮው በ2018 በጀት ዓመት 100.3 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፣ እስከ መስከረም 27/2018 ዓ.ም በተሰበሰበው ዕለታዊ መረጃ መሠረት ከ16 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ተችሏል።

​ይህ አፈጻጸም ቢኖርም፣ በክልሉ ካሉ 22,930 የደረጃ “ሀ” ግብር ከፋዮች መካከል በዚህ ሦስት ወር ውስጥ ግብራቸውን አሳውቀው የከፈሉት 4,004 ብቻ መሆናቸውን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

አቶ ታዘባቸው በርካታ ግብር ከፋዮች አሁንም
ግብራቸውን አሳውቀው እንዳልከፈሉ በመግለጽ፣ በቀሪ ጊዜያት ግብራቸውን አሳውቀው እንዲከፍሉ ጥሪ ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል።

የገንዘብ ሚኒስትር ከዚህ ቀደም በአዲሱ በገቢ ግብር (ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ላይ ማብራሪያ እንደሰጠዉ፤  በየሶስት ወሩ የሚከፈለው ግብር ተፈጻሚ የሚሆነው ግብር ከፋዩ የሂሳብ ሪፖርት ከሚያቀርብበት ወር መጨረሻ ጀምሮ ካለው የሶስት ወር ጊዜ በኋላ በሚኖረው የ30 ቀን ጊዜ ውስጥ ነዉ ማለቱ ይታወሳል።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...