በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 9 ወራት 83,000 ህፃናት ተወልደዋል

Date:

ከሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ዘግይተው የተመዘገቡትን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ324 ሺህ በላይ ህፃናት ተወልደዋል ብሏል፡፡

በሌላ በኩል ኤጀንሲው በተጠቀሰው ጊዜ በከተማዋ ከ5,000 በላይ ሰዎች መሞታቸውን መዝግቤአለው ሲል ነግሮናል፡፡

የሲቪል ምዝገባና የኗሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ምዝገባዎቹን ሲያደርግ በወቅቱ በዘገየ፣ እንዲሁም የጊዜ ገደቡ ያለፈበት፣ እያለ እንደሚመዘግብ ነግሮናል፡፡

በዚህም እነዚህ 83,000 ህፃናት በተወለዱ በሰላሳ ቀን ውስጥ የተመዘገቡ እንደሆኑ እና በወቅቱ የተመዘገቡ መሆናቸውንም ኤጀንሲው አስረድቷል፡፡

ሆኖም በአጠቃላይ በ9 ወር ውስጥ ወቅቱን ጠብቀው ከተመዘገቡት ሌላ በዘገየ እና የጊዜ ገደቡ ያለፈበት ተብለው የተመዘገቡት ጋር ከ324,000  በላይ መሆናቸውንም ሰምተናል፡፡

ተቋሙ ውልደት የሚከናወንባቸው 150 ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ እንደሆነ የነገሩን በሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ውስጥ ምዝገባና መረጃ ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ ናቸው፡፡

ከጋብቻ ጋር ተያይዞ በአጠቃላይ በ9 ወር በወቅቱ የተመዘገቡት 8000 መሆናቸውንም ነግረውናል፡፡

በኤጀንሲው ከተደረገ ምዝገባዎች መካከል አንዱ ፍቺ ሲሆን ወቅቱን የጠበቀ ምዝገባ ያደረጉት 3000  ናቸው ተብሏል፡፡

ይህ በወቅቱ የተደረገ የፍቺ ምዝገባ በኤጀንሲ ከፍተኛ ቁጥር ነው ሲሉ ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡

ወላጆች ለልጆቻቸው በወቅቱ የልደት ሰርተፍኬት እንዲያወጡላቸው እና ለቅድመ ትምህርት ምዝገባም አስፈላጊ በመሆኑ ከወዲሁ እንዲወስዱ ኤጀንሲው ጠይቋል፡፡

ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

” ከ140 በላይ ጠጠር አምራች ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ቆመዋል ” – ማህበሩ

" ካላቸው ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ። ግን መሬቱ መቼ እንደተወሰደባቸው...

ትራምፕ “በኢራን ላይ ሊፈጸም ታቅዶ የነበረውን ጥቃት አንፈጽምም” አሉ

ትራምፕ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ቁልፍ የአሜሪካ አጋር ሀገራት መሪዎች...

በነዳጅ ጭማሪ በኬንያ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ

በኬንያ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ በጸጥታ...

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመስጠት 667 የፈተና ማዕከላት ተዘጋጁ

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ...