በአዲስ አበባ ስያሜ ያልተሰጣቸው 32ሺህ መንገዶች አዲስ እና ዘመናዊ የአድራሻ መለያ ቁጥር ሊሰጣቸው ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የአድራሻ ሥርዓት ዝርጋታ እና አስተዳደር ዳይሬክተር ተመስገን ኃይለዮሃንስ ለኤፍ ኤም አዲስ 97.1 እንደተናገሩት፤ በከተማዋ የሚታወቁ እና ይፋዊ ስያሜ ያላቸው መንገዶች ቁጥር 133 ብቻ ናቸው።
በከተማዋ 32 ሺህ መንገዶች ምንም አይነት ስያሜ እና ቁጥር ያልተሰጣቸው እንደሆኑ ጠቅሰው፤ በአዲስ የአድራሻ ሥርዓት መሰረት ስያሜና መለያ ቁጥር እንደሚያገኙ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ከመንገዶቹ ጋር ትስስር ላላቸው 1 ሚሊዮን ቤቶች አዳዲስ የቤት ቁጥር እንደሚሰጣቸውም ነው የገለጹት።
