የከተማና መሠረተ ልማት ሚንስቴር ዴኤታ አቶ የትምጌታ አስራት እንደገለጹት፤ ፕሮጀክቱ በ407 ሚሊዮን ዶላር በጀት፣ በ126 ወረዳዎች የሚተገበር ነው።
በገጠር በመሬት አቀማመጥና በሌሎች ምክንያቶች ተደራሽ ያልሆኑ አካባቢዎችን በማስተሳሰር ማህበራዊ ግልጋሎት ሰጪ ተቋማትን ለማህበረሰቡ የማዳረስ ዓላማ አለው ተብል ፡፡
በፕሮጀክቱ ከሰባት ሺህ በላይ የገጠር መንገዶች ግንባታ፣ ከ10ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የገጠር መንገድ ጥገና፣ ከሰባት መቶ በላይ የመሻገሪያ ድልድዮች እና እና ከሦስት መቶ በላይ ተንጠልጣይ የእግረኛ መሻገሪያ ድልድዮች ግንባታ ያካትታል ተብሏል ፡፡
ፕሮጀክቱ ከ50 ቢሊዮን ብር በላይ የሚፈጅ ሀገራዊ ሲሆን ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ ከዓለም ባንክ 300 ሚሊዮን ዶላር እንደተገኘና ክልሎች ደግሞ 107 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያዋጡ የዘገበው ኢፕድ ነው።
