ታሜሶል ኮሚኒኬሽን ያዘጋጀው የፋሲካ-ኤክስፖ  ተከፈተ

Date:



የመክፈቻ ስነ ስርዓቱ የፊታችን ማክሰኞ እንደሚከናወን ተነግሯል።

ኤክስፖው “ቴሌ ብር አዲስ ነገር እስከ ፋሲካ 2017 ኤክስፖ” የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።

በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል አስከ ሚያዚያ 11/2017 የሚካሄደው ኤክስፖው ታሜሶል ኮሚኒኬሽን፣ ከታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽን እና ከሊያን ቢዝነስ ግሩኘ ጋር በመሆን አዘጋጅተውታል።

ኤክስፖው ከዚህ ቀደም ከተደረጉ የንግድ ትርኢቶች የተለየ እና ልዩ የሚያደርጉት በርካታ ዝግጅቶች ማቀዱን ተነግሯል።

በቴሌ ብር አዲስ ነገር እስከ ፋሲካ ኤክስፖ ላይ ከ300 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ንግድ ተቋማት ምርት እና አገልግሎቶቻቸውን  ያቀርባሉ ተብሏል።

ከንግድ ተቋማት በተጨማሪ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና በልዩ ትኩረት ለአካል ጉዳተኞች እድል፣ በአካል ጉዳተኞች የተመረቱ ምርቶች ለሽያጭ ይቀርባሉ ተብሏል።

በግብይት ወቅት በቴሌብር ለሚከፍሉ 10 በመቶ ተመላሽ እንደሚያገኙም ዛሬ በተሰጠው መግለጫ ላይ ተነግሯል።

ወደ ኤክስፖ ለሚመጡ ጎብኚዎች የተለያዩ የፆም ምግቦች(በብፌ መልክ) በአንድ ቦታ ተዘጋጅቷል ተብሏል።

በኤክስፖው ላይ አንድ የቤት መኪና፣ የሞባይል ቀፎ፣ ሞተር ሳይክል በሽልማት መልክ እንደሚወጡ ተነግሯል።

ታሜሶል ኮሚኒኬሽን የፋሲካ በዓል ዋዜማ ኤክስፖ ጨረታ ያሸነፈው በ60 ሚሊየን ብር  ነው መባሉ ይታወሳል።

ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...