ትራምፕ ለሦስተኛ ጊዜ ለስልጣን ሊወዳደሩ እንደሚችሉ ተናገሩ

Date:

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ሕገ መንግሥት የፕሬዚዳንትነት ስልጣን የሁለት ጊዜ ገደብ ቢኖርም፤ ለሦስተኛ የሥልጣን ዘመን ሊወዳደሩ እንደሚችሉ በድጋሚ ተናገሩ።  

ትራምፕ ከአሜሪካዉ «ኤንቢሲ» ዜና ወኪል ጋር በደረጉት ቆይታ “እየቀለድኩ አይደለም” ብለዋል።

ትራምፕ ይህን ህልማቸዉን ለማሳካት ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ዘዴዎችንም ጠቁሟል።

እንደ ትራምፕ በሕገ መንግሥቱ 22ኛው  አንቀጽ፤ ሕገ መንግሥታዊ ለውጥ ሳይደረግ ለሦስተኛ ጊዜ ለስልጣን መወዳደር በሕግ የማይቻል እንዲሆን ያደርጋል ብለዋል።

ትራምፕ ሁለተኛ የስልጣን ዘመናቸዉን ከያዙ በኋላ፣  የመንግስት ዘርፎች ላይ ለዉጥ ለማድረግ ከኤሎን ሙስክ ጋር ተባብሮ መስራትን ጨምሮ ታይቶ የማይታወቅ አስፈፃሚ እርምጃዎችን በመተግበር ላይ መሆናቸዉ ይታወቃል።

የትራምፕ ደጋጋፊዎች በበኩላቸዉ፤ በርታ ከዚህ በበለጠ  ማድረግ አለብህ እያሉ አበጀህ ሲሉ ጥሪ እያሰሙ ነዉ። 

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የዓለም የቡና ገበያ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተገለጠ

በዓለም አቀፍ ደረጃ በቡና አቅርቦት ላይ ተፈጥሮ የነበረው ስጋት...

አሜሪካ የኢራንን የጭነት መርከብን መያዟን አስታወቀች

በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን የዘጋችው...

“ቴዲ አፍሮ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ቀይሮታል!” — ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

በ"ወቸው ጉድ" ፖድካስት ላይ እንግዳ ሆነው የቀረቡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ...