አል ዐይን አማርኛ ሥራ ሊያቆም ነው

Date:

ባለቤትነቱ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች መንግሥት የኾነው አል ዐይን አማርኛ የበይነ መረብ የዜና ማሠራጫ ሥራ ሊያቆም ነው ፡፡

የዜና ማሠራጫው በአማርኛ ቋንቋ ዜናዎችንና ዘገባዎችን የሚያዘጋጁ የኢትዮጵያ ዘጋቢዎቹን የቅጥር ውል አቋርጧል ፡፡

ተቋሙ የሠራተኞቹን ውል ያቋረጠው፣ የአማርኛ ዜና አገልግሎቱን አቁሞ የኢትዮጵያ ቢሮውን ዘግቶ ለመውጣት በማሰቡ መኾኑን ተዘግቧል፡፡

ዘጋቢዎቹ ሥራቸውን እየሠሩ ባሉበት ወቅት ምንም ዓይነት ቅድመ ማስጠንቂያ ሳይደርሳቸው፣ በድንገት የሥራ ውላቸው መቋረጡን የሚያመላክት መልዕክት በኢሜይል እንደደረሳቸው ዋዜማ ሰምታለች፡፡

ከአምስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የዜና አገልግሎት የጀመረው አል ዐይን አማርኛ ከትናት በስትያ ጀምሮ ዜናዎችን አላሠራጨም፡፡ የዜና ድረረገጹ በዋናነት ትኩረቱን በመካከለኛው ምሥራቅ ላይ አድርጎ የአገር ውስጥና ዓለማቀፍ ዜናዎችን በአማርኛ ቋንቋ ለኢትዮጵያዊን አንባቢዎች ሲያቀርብ ነበር ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...