አልሸባብ ባደረሰው ጥቃት ቢያንስ 10 ታዳጊዎች ተገደሉ

Date:

በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ለወታደራዊ ምዝገባ ተሰልፈው የነበሩ ታዳጊዎች ላይ በደረሰ የቦምብ ጥቃት ቢያንስ 10 ታዳጊዎች መሞታቸው ተገለጸ፡፡

ታዳጊዎቹ የተገደሉት ዳማንዮ በተባለ ወታደራዊ ካምፕ ላይ የአልሸባብ አሸባሪ ቡድን ባደረሰው ጥቃት መሆኑም ተዘግቧል፡፡

አሸባሪ ቡድኑ ባወጣው መግለጫም ከጥቃቱ ጀርባ እጁ እንዳለ እና እስከ 30 የሚደርሱ ወታደሮችን መግደሉን እንዲሁም ሌሎች 50 ሰዎች ማቁሰሉን ገልጿል።

አልሻባብ በሚጠቀምበት የሬዲዮ ጣቢያ በርካታ አዲስ ምልምል ወታደሮችን ገድለናል ማለቱን እንዲሁም በጥቃቱ ከተገደሉት በተጨማሪ 16 ሰዎች መጎዳታቸውን የሀገሪቱን ፖሊስ ዋቢ አድርጎ የጀርመን ዜና አገልግሎት ዲፒኤ ዘግቧል።

በጥቃቱ ብርቱ ጉዳት ደርሶባቸው በአስጊ ሁኔታ ውስጥ ያሉ በርካቶች መሆናቸውን ተከትሎ የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ተገምቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...

የብሔር ፌደራሊዝምን ለማስቀጠል “የቆረጡ” ተመካካሪዎች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 14ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች የአጀንዳ...

“የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው” ፓትርያርኩ

የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው...