አሜሪካ በሶሪያ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ማንሳቷን ተከትሎ የተለያዩ ተቋማትና ሀገራት ምን አሉ?

Date:

የተመድ ዋና ፀሐፊ ቃል አቀባይ ስቴቨን ዱጃሪች፣ “አሜሪካ በሶሪያ የጣለቻቸውን ማዕቀቦች ማንሳቷ የሶሪያን ህዝብ የአኗኗር ዘይቤ ይቀይራል” ብለዋል።

የሶሪያ ቻምበር ኦፍ ኮሜርስ፣ “የማዕቀቡ መነሳት ኢኮኖሚስቶች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ያበረታታል” ሲል ገልጿል።

የሶሪያ የኢኮኖሚና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ “የሶሪያ ኢኮኖሚ እንደ አዲስ እንዲያንሰራራ አስተዋጽኦ ያደርጋል” ባይ ናቸው።

ኳይት በበኩሏ፣ “ውሳኔውን እደግፋለሁ” ስትል ገልጻለች።

የኦማን ሱልጣን የማዕቀቡን መነሳት፣ “የሚበረታታ ነው” ብለውታል።

የመን ማዕቀቡ መነሳቱ ጥሩ እርምጃ መሆኑን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል ገልጻለች።

የሊቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ “ለጉዳት የተጋለጠውን የሶሪያን ህዝብ ከችግር ለማውጣት የተወሰደ አወንታዊ እርምጃ ነው” ሲል ውሳኔውን ደግፏል።

የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ “አሜሪካ ማዕቀቡን ለማንሳት ያሳየችውን ድጋፍ እንደሚያደንቅ” ገልጿል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ “በመካከለኛው ምሥራቅ ሰላምና ብልፅግናን ማዬት እንፈልጋለን” ሲል አስታውቋል።  

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...